የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደህንነት ከግብፅና ሱዳን ግድቦች የተሻለ ነው -የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር - ኢዜአ አማርኛ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደህንነት ከግብፅና ሱዳን ግድቦች የተሻለ ነው -የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር
አዲስ አበባ ጷጉሜ 02/2012 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ደህንነት ከግብፅና ሱዳን ግድቦች የተሻለ መሆኑን የሱዳን የመስኖ ሚኒስትር ያሲር አባስ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ግድቡ ከሁለቱ ተፋሰስ አገሮች ግድቦች የተሻለ ደህንነት አለው ማለታቸውን የዘገበው ''ሚድል ኢስት'' ጋዜጣ ነው፡፡
''የህዳሴው ግድብ በደህንነቱ ከሱዳን ግድቦች ከግብጹ ሃይ ግድብ የተሻለ መሆኑን በጥናት ተረጋግጧል''ብለዋል፡፡
ሱዳን ጎርፍ እያስከተለባት ባለው አደጋ ባለፈው ሳምንት ለሶስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ማወጇ ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያ ግድቡን ሶስቱን አገሮች የማይጎዳ መሆኑን ደጋግማ ገልጻለች፡፡
ግድቡ ለአገሮቹ ከሚያስገኝላቸው ጥቅሞች አንዱ የጎርፍ አደጋ መቀነስ መሆኑንም ስታስታውቅ ነበር፡፡