ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያን በውጭ አገራት ለሚወክሉ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ

አዲስ አበባ ሀምሌ 6/2010 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኘሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ኢትዮጵያን በውጭ ሀገሮች ለሚወክሉ አምባሳደሮች ሹመት ሰጡ። የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጨምሮ ስምንት አምባሳደሮች ተሹመዋል። በዚህም መሰረት
  1. አቶ ሽፈራው ሽጉጤ
  2. አቶ አለማየሁ ተገኑ
  3. አቶ እሸቱ ደሴ
  4. አቶ አዛናው ታደሰ
  5. አቶ ዮናስ ዮሴፍ
  6. አቶ ድሪባ ኩማ
  7. አቶ ያለው አባተ
  8. አቶ አብዱልፈታ አብዱላሂ
በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት መሾማቸውን የፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። አቶ ድሪባ ኩማ  ዛሬ በአንባሳደርንት እስከተሸሞበት ድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን በማገልገል ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም