ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የሱዳን አቻቸው አብደላ ሃምዶክ ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነዋል

56

ነሃሴ 19/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ሱዳን ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክና የአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

"ስለ ተደረገልኝ ደማቅ አቀባበል ወንድሜ አብደላ ሐምዶክን አመሰግናለሁ" በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን በሚኖራቸው ቆይታ ከአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበትና በሌሎች ቀጣናዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም