መንግስት በአዲስ አበባ እያከናዋነቸው ያለው ፕሮጀክቶች ለእድገት ያለው ቁርጠኝነት ማሳያ ናቸው

324

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9/2012(ኢዜአ) በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች መንግስት ለልማት ስራዎች እያሳየ ያለውን ቁረጠኝነት አመላካች መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመዲናዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

ፕሮጀክቶቹ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠርና የቱሪስት ፍሰትን በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፡፡

ለመሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታና ልማት የቅርብ ክትትል ማድረግ በታለመላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ትልቅ አስተዋጾኦ እንዳለውም ፕሮጀክቶቹ አመላካች እንደሆኑ ገልጸዋል።

አቶ ደገሙ ሙነታ የተባሉ ነዋሪ እንደገለጹት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እያከናወኗቸው ያሉት ፕሮጀክቶች ለአገራዊ እድገት ትልቅ አበርክቶ አላቸው።

ወጣት ሜሮን በላይ በበኩሏ ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የልማት ተጠቃሚነትን እንደሚያረጋገጡ አመልክታለች።

አቶ ተስፋየ ጸኃየ ”መንግስት በቅርሶች ላይ እድሳት በማድረግና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ነድፎ በማጠናቀቅ ለእይታ ክፍት ማድረጉ ለልማት ቁርጠኛ መሆኑን ያሳያል” ብለዋል፡፡

መንግስት እያከናወናቸው ያሉት እነዚሁ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ማራኪ የከተማን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለአገሪቱ እድገትና ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም መንግስት መሰል ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በሌሎች የክልል ከተሞችም የልማት ስራውን ማስፋፋት እንዳለበት አስተያየት ሰጪዎቹ መክረዋል፡፡