የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ በመጪው ሰኞ ይጀመራል

58

ሐረር ነሐሴ 9 / 2012(ኢዜአ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አስታወቁ።

አፈ ጉባኤዋ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ለሁለት ቀናት የሚቆየው የምክር ቤቱ  ጉባኤ የ2012 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

ለክልሉ የ2013 የስረ ዘመን ማስፈጸሚያ  ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ አባላት  ይቀርባል ብለዋል።

የቀረቡትን የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና ረቂቅ በጀቱ  ላይ የምክር ቤቱ አባላት ከተወያዩበት በኋላ እንደሚያጸድቁት ይጠበቃል።

እንዲሁም  የምክር ቤቱ ጉባኤ  የክልሉ አስፈጻሚ አካላት የቀጣይ ስራ ትኩረት አቅጣጫ እንደሚመለከት የገለጹት አፈ ጉባኤዋ  አዳዲስ ሹመቶች  እንደሚኖሩም  ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም