ዘመናዊ የክትትልና ግምገማ ስርዓት ይፋ ሆነ

118

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 7/2012 (ኢዜአ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የዲጂታል የክትትልና ግምገማ ስርዓት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ አስጀምሯል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በመድረኩ ተገኝተው ሰራውን በይፋ አስጀምረዋል።

ይህ ዘመናዊ ስርዓት የ10 ዓመቱን መሪ የልማት ዕቅዱን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እቅዶችንና የልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ውጤታማነት ለማገዝ እንዲያስችል ተደርጎ በአገር ውስጥ ባለሙያዎች የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።

ዝርዝር ዜናውን እንደደረሰን የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም