በኢትዮጵያ ተጨማሪ 584 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 5/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 11 ሺህ 881 የላቦራቶሪ ምርመራ 584 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ20 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 24 ሺህ 175 ደርሷል።

የተጨማሪ 20 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ፤ በአጠቃላይ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 440 መድረሱም ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 190 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ 13 ሺህ 037 ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው መሆኑ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት 285 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን እስካሁን 10 ሺህ 696 ሰዎች አገግመዋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ 520 ሺህ 891 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም