በፈረንሳይ የፊት ጭምብል አለመጠቀም 160 ዶላር ያስቀጣል

72

ነሀሴ 5/2012 በፈረንሳይ  የፊት ጭምብል  የማይጠቀሙ  ሰዎች የ160 ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተባለ፡፡

ፓሪስ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመግታት ሰዎች በብዛት በሚገኙባቸው ቦታዎች   የፊት ማስክ አለመጠቀም  160 የአሜሪካን ዶላር የሚያስቀጣ  ህግ አጸደቀች፡፡

ያለ ፊት ጭምብል መንቀሳቀስ የሚያግደው ህግ ከዋና ከተማዋ ፓሪስ በተጨማሪ  በፈረንሳይ በ1 ሺህ 5 መቶ ከተሞች ላይ ተግባራዊ እንደሚሆንም ነው የተጠቀሰው፡፡

አስገዳጁ ህግ ተግባራዊ ከሚደረግባቸው መካከል  የሞንትማርተር ሰፈር   እና  የሳይን  የወንዝ ዳርቻዎች ጎብኝዎች  እንዲሁም በእምነት ስፍራዎች የፊት ጭምብሎች በጠቀም  ካለባቸው  ቦታዎች ተጠቃሽ ናቸው ፡፡  

ቀደም ሲል የፊት ጭምብልን  ስንጠቀም የነበረ  ቢሆንም ሰዎች   በሚበዙበት ስፍራዎች  ጭምብልን  መጠቀም የሚስገድደው  አዲሱ ህግ መተግበሩ   ቫይረሱን  ለመከላከል ያግዛል  ያሉት የፓሪሱ   ነዋሪ ደልፊን  ናቸው፡፡