ተጨማሪ 773 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

121

 አዲስ አበባ  ነሀሴ 4/2012 (ኢዜአ) ተጨማሪ 773 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

ባለፉት 24 ሰዓታት በኢትዮጵያ በተደረገው 11 ሺህ 039 የላቦራቶሪ ምርመራ 773 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 23 ሺህ 591 ደርሷል።

እንዲሁም የተጨማሪ 13 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ፤በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 420 መድረሱም ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 164 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ይገኛሉ፤ 12 ሺህ 758 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር እንደሆነ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት204 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 10 ሺህ 411 ደርሷል፡፡

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 509 ሺህ 010 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።