የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

70
ጅግጅጋ ሀምሌ 4/2010 የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ጀመረ፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ የክልሉ መንግስት የ2010 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ይገመገማል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኦዲት መስሪያ ቤት ዓመታዊ ሪፖርት እንዲሁም የክልሉ የ2011 ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ 195 የምክር ቤቱ አባላት መገኘታቸው ታውቋል ፡፡            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም