በዛሬው እለት 459 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎችም ህይወት አልፏል

31

አዲስ አበባ ሐምሌ 29/2012 (ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 319 የላቦራቶሪ ምርመራ 459 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎችም ህይወት አልፏል።

የጤና ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ 319 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 459 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎችም ህይወት አልፏል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 459 ሺህ 746 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 20 ሺህ 336 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

እስካሁን በድምሩ የ356 ሰዎችም ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 358 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል።