588 ሰዎች ኮሮና ሲገኝባቸው ፤የ7 ሰዎች ሕይወትም አልፏል

108

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በ 8 ሺህ 201 በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 588 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አሁን 19 ሺህ 877 ደርሷል።

በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው ያለፈውን ሰባት ሰዎች ጨምሮ እስካሁን በኢትዮጵያ የ343 ሰዎች ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 309 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

እስካሁን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 8 ሺህ 240 ደርሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም