በኢትዮጵያ ተጨማሪ 583 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኘባቸው፤ የ26 ቱ ህይወት አለፈ

33

አዲስ አበባ (ኢዜአ) 27/2012በኢትዮጵያ ተጨማሪ 583 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ26 ሰዎች ህይወትም አልፏል

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 583 በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ በቫይረሱ ምክንያት የ26 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 289 ደርሷል።

እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ባለፉት 24 ሰዓታት የ26 ሰዎች ሲያልፍ በዚህ በሀገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 336 መድረሱን ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።

በአሁን ወቀት በሀገሪቱ 145 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተነግሯል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 330 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆንአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7ሺህ 931 ደርሷል።

በአጠቃላይ በኢትዮዽያ 444 ሺህ 226 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።