ትምህርት ቤቶች ከነሐሴ መጨረሻ ሳምንት በፊት ምዝገባ ማካሄድ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

61

አዲስ አበባ (ኢዜአ) 27/2012 ከነሃሴ መጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።


አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ለማድረግ ወላጆችን እያስገደዱ መሆኑ እና ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።


የትምህርት ሚኒስቴር የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ መጨረሻ በፊት ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ እንማይቻል እና ይህንን ወሳኔ አልፈው ምዝገባ በሚያካሂዱ ትምህርት ቤቶች ላይም አስፈላጊው የዕርምት እርምጃ እንደሚወሰድ ማስጠንቀቁን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


የምዝገባው የግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተፈለገው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት የ ቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ወላጆች ከተሳሳተ መረጃ እራሳቸውን በመጠበቅ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በመከላከልእና መንግስት ትምህርት እንዲጀመር ሲያሳውቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አውቀው ልጆቻቸው በእጃቸው ላይ የሚገኙትን የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዲያነቡና ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም