የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርሰቲያን ልዑክ በአጋርፋ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኞችን ጉበኘ

62

አዲስ አበባ ሐምሌ 27 /2012 ዓ.ም (ኢዜአ).ከኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርሰቲያን የተወጣጣ የልዑካን ቡድን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖች ያሉበትን ሁኔታ ጎበኝቷል። 

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንደሳን ግድያ ተከትሎበወረዳው ከ1 ሺ 400 በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የማህበረ ምዕመናን ሽማግሌዎች አባልና የክርስቲያን በጎ አድራጎት ማህበራት ህብረት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጉሱ ለገሠ እንደገለፁት የጉብኝቱ አላማ ተጎጂዎች ያሉበትን ሁኔታ ከማየት ባሻገር ችግሩ የደረሰባቸውን ሰዎች ቀጥታ በማግኘት የተቻለውን እርዳታ ለማድረግ እንዲሁም አብሮነታቸውን ለማሳየት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑምኮሚቴው የተፈናቃዮችን ጉዳትና ያሉበትን ሁኔታ በመገንዘብ ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ዶክተር ንጉሱ ያስረዱት።

የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ በበኩላቸው ለረጅም ዓመታት አብሮ የኖረን ማህበረሰብ ማጋጨት የኢትዮጵያዊያን ልምድ ሳይሆን የጥፋት መልእክተኞች ተግባር ነወው ብለዋል።

በሌሎች የዓለም ሃገራት ሲሰሙት የነበረን አረመኔያዊ ተግባር በኢትዮጵያም በማየትና በመስማታቸው ማዘናቸውን ገልጸው መንግሥት እንዲህ አይነት እኩይ ተግባር የሚፈፅሙ አካላትን  እርምጃ በመውሰድ ጠንካራ አቋም መያዝ አለበት ብለዋል።

ከአጋርፋ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል በነበረው ግርግር የተፈናቀሉት ወይዘሮ በሃይልዋ ተሻለ በግጭቱ ባለቤታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለውባቸዋል።

ከባለቤታቸው ሞት በተጨማሪ ቤት ንብረታቸው ወድሞባቸው አሁን ላይ ተፈናቅለው ይገኛሉ።

በዚህም ተደራራቢ ጉዳት እንደገጠማቸው ተናግረዋል።

የ80 ዓመቱየእድሜባለፀጋ አቶ በላይሁን በቀለም ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ በእሣት መጋየቱ ለመፈናቀል መገደዳቸውን አስረድተዋል።

በግርገሩጉዳትየደረሰባቸውዜጎችመንግስት ገዳዮችንና አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርብላቸውም ጠይቀዋል፡፡

የህግ የበላይነት ተረጋግጦ ወደ ቀያቸው ተመልሰው የግብርና ስራቸውን እንዲያከናውኑም መንገስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል።

የአጋርፋ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ሽመልስ ቶሎሣ እንደገለጹት በነበረው ሁከት በአምቤልቱ ቀበሌ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 59 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

በአሁኑወቅት በግርግሩ የተዘረፉ ሃብትና ንብረቶችን በማስመለስ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ የተፈናቀሉ ወገኞችን ወደ ቀያቸው ለመመለስም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈፀም ህግ የማስከበር ስራው ተጠናከሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርሰቲያን ልዑካን ቡድንበሐረር እና ሻሸመኔ ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም