በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት እምርታ አሳይቷል

149

ሐምሌ 27/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት እምርታ በማሳየት ላይ መሆኑን ተገለጸ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬታሪያት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከአናዱሉ ኤጀንሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ የነበሩ የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን ለማሻሻል ተሰርቷል፡፡

መንግስት በወሰዳቸው የለውጥ ስራዎች ለአመታት የተከማቹ ችግሮችን ለመፍታት የተደረገው ጥረት ኢትዮጵያን በብዝሀነትና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ በአለማቀፍ ደረጃ ተቃባይነት እንድታገኝ አስችሏታል፡፡

የኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚው ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እ.አ.አ 2018 በኢህአዴግ ውስጥ በተደረገው ለውጥ ወደ ሀላፊነት መምጣታቸውን ያስታወሱት አቶ ንጉሱ በለውጡም ነፃና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ ማቋቋም፣ የፍትህ አካላት በገለልተኝነት ማደራጀት፣ የሰብአዊ መብት ማስጠበቅና የፕሬስ ነፃነት እንዲኖር መገረጉን ተናግረዋል፡፡

በርካታ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸው፣ የታጠቁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ አገር መግባታቸውና የፖለቲካ ብዝሃነት እንዲኖር መደረጉንም አክለዋል፡፡

ኢህአዴግ በሚል ስያሜ በአራት እህት ድርጅቶች ሲመራ የነበረው ድርጅት የህዝብን ጥቄዎች ለመመለስ በአዲስ መልክ ማደራጀት በማስገደዱ የሀገሪቱን 8 ክልሎች በማካተት ብልፅግና ፓርቲ ቢመሰረትም ህወሃት ሂደቱን በመቃወም እራሱን ማግለሉን ተናግረዋል፡፡

የህወሃት ባለስልጣናት በወንጀልና በሙስና የሚጠረጠሩ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ማፈናቸውን አስታውሰዋል አቶ ንጉሱ ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም