በአንድ ጀምበር 2 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

56

ሀምሌ 26/2012(ኢዜአ) በአዲስ አበባ በአንድ ጀምበር 2 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ተጀመረ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ዛሬ ማለዳ ከኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል፡፡

በአዲስ አበባ በአንድ ጀምበር ብቻ 2 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ከማለዳ ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ማለዳ ላይ ከኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር ጀሞ አካባቢ በሚገኘው የቡና ስፖርት ክለብ ሜዳ ዙሪያ ችግኝ ተክለዋል፡፡

በቀጣይም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የአረንጓደ አሻራቸውን እንደሚያሳርፉ ይጠበቃል።

በዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ለምግብነት የሚውሉ አትክልት ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሁለት ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉ ይሆናል።

የችግኝ ተከላው የከተማዋ ነዋሪዎች በስፋት ተሳትፈውበት በመከናወን ላይ መሆኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም