ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚደንት ልዩ መልዕክተኛ አነጋገሩ

56

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 22/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳኑን ፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ልዩ መልዕክተኛ ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ  ሱዳን  ፕሬዚደንት  ሳልቫ ኪር ልዩ  መልዕክተኛ  ኒሃል ዴንግ ኒሃልን በዛሬው እለት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸውም በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በተለይም ከኢኮኖሚ ልማት፣ ሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በመተባበር ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።

በቀጠናዊ የትስስር ጥረቶች ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም