የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777 የጭነት አውሮፕላን የእሳት አደጋ ደረሰበት

 አዲስ አበባ  (ኢዜአ) ሀምሌ 15/2012  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777 ኢቲ ኤ አር ኤች እቃጫኝ አውሮፕላን የእሳት አደጋ እንደደረሰበት አየር መንገዱ አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ቦይንግ 777 ኢቲ ኤ አር ኤች እቃጫኝ አውሮፕላን የእሳት አደጋ የደረሰበት በቻይና ሻንጋይ አውሮፕላን ማረፊያ ጭነት እየጫነ ባለበት ወቅት ነው፡፡

የእሳት አደጋው በአብራሪውም ሆነ በአየር መንገዱ ሠራተኞች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማድረሱን ተጠቁሟል፡፡

አውሮፕላኑ ጭነቶችን ከሻንጋይ ወደ ሳኦ ፖሎ - ሳንጎጎ ለማጓጓዝ በመደበኛነት የጭነት አገልግሎት እየሰጠ እንደነበር ታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በመጣራት ላይ ነው፡፡

በአውሮፕላኑ ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠርም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ኢትዮጵያ በትብብር መስራቷን መግለጫው አያይዞ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም