በኦሮሚያ ክልል ግንባታቸው ተጠናቆ የተመረቁ ፕሮጅከቶች ህዝቡ በመንግስት ላይ ያለውን አመኔታ ያጠናከረ ነው-- ዶ/ር ግርማ አመንቴ

72

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/2012(ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ግንባታቸው  ተጠናቆ በዚህ አመት  የተመረቁ ፕሮጅክቶች አብዛኞቹ  የገጠር አካባቢ  ያማከሉ  መሆኑን  በምክትል ፕሬዝዳንት ማእረግ የገጠር ክላስተር አደረጃጀት አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ ገለጹ።

ዶክተር ግርማ  የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም አስመልክቶ ዛሬ ለሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅት እንዳሉት 2012 ዓ.ም የተጀመሩት ፕሮጀክቶች የሚጠናቀቁበት አመተ  ተብሎ ወደስራ መገባቱን ገልጸው። ፕሮጀክቶቹ በሶስት ክፍሎች እንደሚከፈሉም ጠቅሰዋል።

ከዚህም ውስጥ የመጀመሪያዎቹ  1358 የንጹህ መጠጥ ዉሃ  ፕሮጀክቶች ለግንባታቸውም  1 ነጥብ 2  ቢሊዮን ብር  ወጪ ተደርጎባቸዋል።

ፕሮጀክቶቹ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

በክላስተሩ ሲሰራ የነበረው  35 ድልድዮችና  አንድ  የመንገድ  መሆኑንና ለዚህም   473 ሚሊዮን ብር  የግንባታ ወጪ  ነው፡፡

ዶክተር ግርማ አክለውም  በ1 ነጥብ 5  ሚሊዮን ብር ወጪ  የተገነቡ  የመስኖ ፕሮጀክቶች መሆኑንና  48 ሺህ ሰዎችን ማገልገል የሚችል ነው ብለዋል ።

በቀጣይም  እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ የሚጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም የጠቆሙት ዶክተር ግርማ፤ለስኬቱ ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ማስቀመጥ፣ እቅድ በጊዜ ማዘጋጀትና ህዝቡን ማሳተፍ ነው  ብለዋል፡፡

የተመረቁት ፕሮጀክቶቹም  ህዝቡ  በመንግስት ላይ  ያለውን አመኔታ የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል ።

የተመረቁት ፕሮጀክቶቹ በገንዘብም ሆነ በብዛት የገጠሩን ማህበረሰብ ያማከሉ  የልማት ስራዎች መሆኑን  ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም