አዳዲስ ተጨማሪ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ---ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

139

ወንጪ፣  ሰኔ 22/2012 (ኢዜአ) ከነባር የቱሪዝም መዳረሻዎች በተጨማሪ አዳዲስ ለማመቻቸት እየተሰራ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ገለጹ።

ሚኒስቴሩና በዘርፋ ካሉት ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በወንጪ ሀይቅ አካባቢ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ  ተከላ መርሃ ግብር እያካሄዱ ነው።


በዚህ ወቅት  የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው እንደተናገሩት ኢትዮጵያ  ከነበር የቱሪዝም መዳረሻዎች በተጨማሪ ለምተው ለአለም ቅርስነት ለመዘገብ የሚችሉ ብዙ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች አሏት።


ከነዚህም  በአሮሚያ  ደቡብ ምዕራብ ዞን የሚገኙት  አዳዲ ማሪያም ፣ መልካ ቁንጥሬ እና  የወሊሶ ፍል ውሀ  ጠቅሰዋል።


በመልካ ቁንጥሬ የተጀመረው የሚኒስትሩና ተጠሪ ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር በወንጪ ሃይቅ አካባቢም  የቀጠለው  የቱሪዝም መስህቦችን መልሶ የማልማቱ አንዱ አካል ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያ ሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው ተቋሙ  በዘርፋ በማሰልጠን ፣ በማማከር፣ በጥናትና ምርምር ረጅም እድሜ ማስቆጠሩን ተናግረዋል።

ተቋሙ በዘርፋ ከተቋቋመው የአረንጓዴ አሻራ  ኮሚቴ ጋር ሆነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያካሄደ ነው ብለዋል


ይህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን  ካለፈ በኋላ የሚከናወኑ የቱሪዝም ማነቃቂያ ስራዎች አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም