ተቋማቱ ችግኞችን ተከሉ

55

ዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2012 (ኢዜአ) የባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር የራይድ ትራንስፖርት ባለቤት ከሆነው ሀይብሪድ ዲዛይንስ ጋር በጋራ በመሆን በገላን አካባቢ ዛሬ ችግኞችን ተከሉ።

የዐረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የተካሄደው በገላን ከተማ በሚገኘው ራይድ ፓርክ በተባለ ቦታ ላይ ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ችግኞችን መትከል ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሄንንም  ደግሞ በተግባር ሲታይ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል ብለዋል።

ኅብረተሰቡም ችግኞቹ የራሱ መሆናቸውን በመገንዘብ እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርግላቸው  አሳስበዋል።

የራይድ ትራንስፖርት ድርጅት ሥራአስኪያጅ ወይዘሪት ሳምራዊት ፍቅሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ ያደረጉት ጥሪ በመርሐ ግብር ለመካፈል እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።

ድርጅታቸው አምና በዚሁ አካባቢ የተከላቸው 10 ሺህ ችግኞች 98 በመቶ መጽደቃቸውን ገልጸዋል።

ችግኞቹ  ዓመቱን ሙሉ እንክብካቤ  እንደተደረገላቸውም አስታውቀዋል።

በዚህም ለአካባቢው ሰዎች ሥራ መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በአሁኑ ክረምትም 3 ሺህ ችግኞች እንደሚተክሉ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

ከነዚህም ውስጥ ከተወሰኑ አገር በቀል ዛፎች ውጭ ሲሆኑ፤የተቀሩት ለምግብነት የሚውሉ ፍራፍሬዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በዘንድሮው የክረምት ወቅት አምስት ቢሊዮች ችግኞች ለመትከል ታቅዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም