ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

180

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2012(ኢዜአ) የአፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በልማት ፕሮጀክቶች፣ በኢትዮጵያና በፈረንሳይ ግንኙነት እንዲሁም ኮቪድ19ን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ተወያይተናል” ብለዋል።

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ የምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።