የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቢላሉል ሀበሻ ማህበረሰብ ሙዚየምን ጎበኙ

142

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2012(ኢዜአ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቢላሉል ሀበሻ የማህበረሰብ ሙዚየም ጎበኙ።

ሙዚየሙ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ  የሙስሊም ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የያዘ ነው።

በሙዚየሙ በእስልምና እምነት  ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ  ሼኮችና ኡለማዎች ምስልና ታሪክ ይገኛል።

አቶ ኃይለማርያም በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ ያሏትን በርካታ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማስተዋወቅ ይገባል።

በተለይ ማህበረሰቡ ያሉትን ያልተነገሩና ሊነገሩ የሚገባቸው ባህላዊና ታሪካዊ ሁነቶች ለማስተዋወቅ እንዲተጋ አሳስበዋል።

አቶ ኃይለማርያም ጉብኝቱን ያደረጉት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና በቱሪዝም ዘርፍ ከሚገኙ አካላት ጋር በመሆን ነው።