ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸነፈ

139

ሰኔ 19/2012 (ኢዜአ) ከሊቨርፑል ከ30 ዓመት ብኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አነሳ፡፡

በትላንትናው እለት በፕሪምር ሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረው  ማንችስተር ሲቲ      በቼልሲ 2 ለ 1 መሸነፉን ተከትሎ ሊቨርፑል ከ30 ዓመታት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለድል ሆኗል፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን በ23 ነጥቦች ልዩነት የሚመራው ሊቨርፑል ሰባት ቀሪ ጨዋታዎች እያሉ ነው የዋንጫ ባለቤት መሆን የቻለው፡፡

ሊቨርፑል በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ ታሪካዊ ከሚባሉ ክለቦች አንዱ ቢሆንም ሊጉ እአአ 1989/90 እንደ አዲስ ከተዋቀረ ወዲህ የመጀመሪያ ዋንጫው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ እና ቼልሲን መካከል የተደረገውን የ90 ደቂቃ ፍልሚያ  በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩት የሊቨርፑል ደጋፊዎች ምሽቱን በአንፊልድ ስታዲየም ዙሪያ ተሰባስበው ደስታቸውን ሲገልጹ አድረዋል፡፡

ሊቨርፑል በዘንደሮው የሊግ ውድድር በቀሪ ጨዋታዎች ተጨማሪ ክብረወሰኖችነ ሊሰብር እንደሚችል የእግር ኳስ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ከእነዚህም መካከል በሜዳው ብዙ ማሸነፍ፤በሊጉ በርካታ ነጥቦችን መሰብሰብ ይገኙበታል፡፡

የአሁኑ ዋንጫ ለሊቨርፑል 19ኛው  መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም