የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በመቀሌ ለሚገኙ 60 አረጋውያን ሴቶች የ60 ሺ ብር ድጋፍ አደረገ

49

መቀሌ ሰኔ 17/2012 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በመቀለ ከተማ ለሚገኙ 60 አረጋውያን ሴቶች የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገለፀ ።   

ፌደረሽኑ በመቀሌ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋውያን ሴቶች  ያበረከተው የ60 ሺህ ብር ድጋፍ በትግራይ  ክልል ሴቶች ፌደሬሽን አማካኝነት እንዲደርሳቸው አድርጓል።

የትግራይ ክልል ሴቶች ፌደሬሽን የስራ አስፈፃሚ አባል ወይዘሮ ገነት ኪዳነ እንደገለጹት በፌዴሬሽኑ ድጋፍ ከተደረገላቸው 60 ሴት አረጋውያን መካከል 20ዎቹ  አካል ጉደተኞች ናቸው ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሰርተው ኑሮአቸውን ለመግፋት የተቸገሩ አረጋውያን  ሴቶች በነብሰ ወከፍ አንድ ሺህ ብር እንዲደርሳቸው ተደርጓል ።

 ፌደረሽኑ ያደረገው ድጋፍ በጣም በችግር ውስጥ ለሚገኙ እናቶች መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ገነት ለፌደረሽኑ ምስጋና አቅርበዋል።

 የኢትዮጵያ ሴቶች ፌደሬሽን ያደረገልን ድጋፍ በኑሮአችን ላይ ትርጉም አለው ያሉት ደግሞ ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ዘውዱ መረሳ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም