የግድቡን ጉዳይ ወደ ፀጥታው ም/ቤት መውሰድ ፋይዳ የለውም - ክራይስስ ግሩፕ

62

ሰኔ 17/2012(ኢዜአ) የግድቡን ጉዳይ ወደ ፀጥታው ም/ቤት መውሰድ ፋይዳ የለዉም ሲል ዓለምአቀፉ ክራይስስ ግሩፕ አስታወቀ።

በግጭቶች ላይ የሚሰራው ዓለምአቀፍ ተቋም ክራይስስ ግሩፕ ግብጽ የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጉዳይ ወደ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት መውሰዷ ችግሩን ለመፍታት መፍትሔ አይሆንም ብሏል።

ተቋሙ እንዳለው በግድቡ የውኃ ሙሌት እና ልቀትም ሆነ በወንዙ ዘላቂ አጠቃቀም ላይ መፍትሔው በውይይት በሚደረስ ስምምነት ብቻ ነው ሲል አስታውቋል።

ተቋሙ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው በህዳሴው ግድብ ላይ በሦስቱ ሃገሮች የተፈጠረው ውዝግብ በአስቸኳይ በድርድር መፈታት ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ 3ቱ ሃገሮች እንደገና ወደ ውይይት እንዲመለሱና ሌሎች አካላትም ለድርድሩ ስምረት በጎ ተፅእኖ በማድረግ እንዲረዱ ጥሪ አቅርቧል።

ተደራሪ ሀገራቱም ከጠባብ ብሄራዊ ጥቅም እና ከግል የፖለቲካ ፍላጎት ወጥተው በጋራ ተጠቃሚ በሚሆኑበት የትብብር መንፈስ ከስምምነት መድረስ እንደሚኖርባቸው የጠቆመው መግለጫው፤ ለዚህም ቀደም ሲል እኤአ በ2015 ሦስቱ ሀገሮች በጋራ ተጠቃሚነት መርሆች ላይ የደረሱበትን ስምምነት መሰረት ማድረግ እንደሚኖርባቸው ማሳሰቡን የጀርመን ድምፅ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም