ግብፅ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃወሙ - ኢዜአ አማርኛ
ግብፅ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃወሙ

ሰኔ 16/2012(ኢዜአ) ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር ተቃውመውታል።
የአረብ ሊግ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ በዛሬው እለት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የአረብ ሊግ በስብሰባው ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለአረብ ሊግ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብን ጨምሮ የሊቢያ ጉዳይንም በመመልከት ላይ መሆናቸውን የፋና ዘገባ ያመለክታል።
በዚህ ስብሰባ ላይም የሊጉ አባል ሀገራት የሆኑት ጅቡቲ፣ ሶማሊያና ኳታር የግብፅን ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ግብጽ ያቀረበችውን የውሳኔ ሀሳብ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል።