ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ትብብር አስፈላጊ መሆኑ ነው...ኬንያውያን ምሁራን

73

 ሰኔ 16/2012 (ኢዜአ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ እንደሚያስተሳስር ኬንያውያን ምሁራን ገለፁ።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ልማት እና ውህድት ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ የዙም የገፅ ለገፅ ውይይት አዘጋጅቷል።

ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ተፈጥሮኣዊ ኃብት የማንንም ፈቃድ እና ችሮታ ሳያስፈልጋቸው የማልማት መብት እንዳላቸው ምሁራኑ እንደሚገነዘቡ ገልፀው በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረሙ ስምምነቶች ተቀባይነት የሌላቸው እና ኋላ ቀር ሰነዶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ነጻነት ያለው ማንኛውም ሀገር የሚቀበለው ስምምነት አይደለም። ተወያዮቹ የቀጠናው ሕዝቦች ከአትዮጵያውያን ጋር ነን፤ ኢትዮጵያም ብቻዋን አይደለችም ብለዋል።

በውይይቱ በናይሮቢ ዪኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር ፕሮፌሰር ሙሳምባይ ካቱማንጋ፣ የቀድሞ የኬንያ ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ፋራህ ማዓሊም፣ የቀድሞ የናይሮቢ ከተማ ከንቲባ እና የኢትዮጵያ-ኬንያ ወዳጅነት ማህበር ሊቀ መንበር ጆ አኬች እንዲሁም የቀድሞ የኬንያ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊ እና የቀጠናዊ ውህደት እና ልማት ጉዳዮች ተንታኝ አህመድ ሃሺ ተሳትፈዋል።

ምንጭ፡-በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም