ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

74
አዲሰ አበባ ሐምሌ 2/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤርትራ ሲያካሂዱት የነበረውን የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትም አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። ትናንት ማለዳ አስመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ይታወሳል። በቆይታቸውም ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ላለፉት 20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በሚቀጥልበት መንገድ መክረዋል። ወደብ መጠቀምን ጨምሮ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር፣ ዜጎች በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉና የሁለቱ አገራት አየር መንገዶች መደበኛ በረራ እንዲያደርጉ መሪዎቹ ከስምምነት ደርሰዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም