በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ9 ሚሊዮን አለፈበዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አሃዝ 9 ሚሊዮን 79 ሺህ 452 ደረሰ - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ9 ሚሊዮን አለፈበዓለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች አሃዝ 9 ሚሊዮን 79 ሺህ 452 ደረሰ

ሰኔ 16/2012(ኢዜአ) ከተቀሰቀሰ ስድስት ወራትን ያሳለፈው ይሂው ቫይረስ መላው ዓለምን አዳርሶ 9 ሚሊዮን 79 ሺህ 452 ሰዎችን አጥቅቶ ከ474 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ቢቢሲ ዘግቧል።
በሽታው በወረርሽኝነት የተከሰተባት ቻይና በሦስት ወራት ውስጥ በሽታውን መቆጣጠር ብትችልም ቫይረሱ በፍጥነት ወደ አውሮፓ ከዚያም ወደ ሰሜን አሜሪካ ተሻግሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የበሽታው ታማሚ ሆነዋል።
ከዓለም አገራት ውስጥ ከፍተኛው በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሏት አገር አሜሪካ ስትሆን 2 ሚሊዮን 289 ሺህ 168 ህሙማንን እንዳገኘች እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ የመዘገበች ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል 1 ሚሊዮን 083 ሺህ ,341 ዜጎቿ በበሽታው መያዛቸውን ዘገባው አስታውሷል።
በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ አውሮፓንና እስያን የምታካልለው ታላቋ ሩሲያ 591 ሺህ 456 ሰዎች በሽታው እንዳለባቸው ያሳወቀች ሲሆን፤ ከአንድ ቢሊየን በላይ ሕዝብ ያላት የእስያ አገር ሕንድ 425 ሺህ282 ሰዎች ላይ በሽታውን አግኝታለች።
በእነዚህና በሌሎችም አገራት በበሽታው መያዛቸው የሚረጋገጥ ሰዎች ብዛት በየደቂቃው እየጨመረ እንደሚሄድ እና ከ474 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ያመለክታል።