በ24 ሠዓታት የምርመራ ውጤት 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

54

አዲስ አበባ ሰኔ 15/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሠዓታት በተደረገ 3 ሺህ 238 የላቦራቶሪ ምርመራ 131 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ የአንድ ሰው ሕይወትም አልፏል። 

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዕለታዊ መግለጫ እንዳመለከተው ተጨማሪ 84 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በዛሬው ሪፖርት ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 98ቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ 4 ከሶማሌ፣ 16  ከኦሮሚያ፣ ሶስት ከአፋር፣ አንድ ከአማራ፣ ሁለት ከጋምቤላ፣ ሶስት ከደቡብና አንድ ከትግራይ ክልሎች እንዲሁም ሶስት ሰዎች ከድሬዳዋ መሆናቸው ተዘርዝሯል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 94 ወንዶችና 37 ሴቶች ከሁለት እስከ 80 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች 130ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አንዱ የውጭ አገር ዜጋ ነው።

ከጠቅላላው የላቦራቶሪ ምርምራ 26ቱ ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ከማኅበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 75 ደርሷል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 84 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን 79 ከአዲስ አበባ፣ ሁለት ከኦሮሚያ፣ ሁለት ከትግራይና አንድ ከደቡብ ክልሎች ናቸው።

እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 297 ሲደርስ 38 ሰዎች በፅኑ ሕሙማን ክትትል ክፍል እንደሚገኙ ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም