የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ ተሰብስበው የተገኙ 13 ግለሰቦች ተቀጡ

52

አዳማ ሰኔ 15/2012 (ኢዜአ)በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ ተሰብስበው የተገኙ 13 ግለሰቦች መቀጣታቸው ፖሊስ አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተቀጡት አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን መመሪያ በመተላለፍ ነው።

በአዳማ ወረዳ ዲቢቢሳ ወጭላፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በሚገኘው በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ ከአራት ሰው በላይ ሆነው ተሰብስበው በመገኘታቸው ለቅጣት እንደዳረጋቸው ኮማንደሩ ተናግረዋል።

በዚሀም 13ቱ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው 2ሺህ ብር መቀጣታቸውን የገለጹት ኮማንደር አስቻለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የወጣውን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚነት ከፀጥታ አካላት ባለፈ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል መተባባር እንደሚገባው አሳስበዋል ።

የኮሮና በሽታ የስርጭት መጠን በአሳሳቢ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ይህን ተግንዝቦ ከበሽታው ራሱን መጠበቅና  ከቅጣት መዳን እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም