ጀርመን ለአደጋ ተጋላጭ የአፍሪካ ገበሬዎች ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገች

60

ሰኔ 15/2012(ኢዜአ) ጅርመን ለአደጋ ተጋላጭ አፍሪካውያን ገበሬዎች 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች ፡፡

የጀርመን የኢኮኖሚ ኮፕሬሽንና ልማት ሚኒስቴር በተባበሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኩል ለ1.2 ሚሊዮን አፍሪካውያን ገበሬዎች ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ድጋፉ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ አፍሪካውያን ገበሬዎችን  የአየር ንብረት አደጋ መድን ለመስጠት በማሰብ ነው የተደረገው ሲል የአለም ምግብ ፕሮግራም ጽፏል ፡፡

ወቅቱ አገራት ኮቪድ 19 ኮሮናን ለመከላከል ትኩረት ያደረጉበት ሲሆን ድርቅን የመሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ሲደረግ የነበረው ጥረት ግን ተቀዛቅዟል፤ ይህንን ተከትሎም ድጋፉ እንደተደረገ በአለም የምግብ ፕሮግራም የአየር ንብረትና የተፈጥሮ አደጋ መከላከል ሃላፊ ጌርኖት ላጋንዳ ተናግረዋል፡፡

አሁን ጀርመን ያደረገቸው ደጋፍም በዋናናት በሞሪታንያ ለሚገኙ 108 ሺ፣ለቡርኪናፋሶ 45ሺ፣ ለጋምቢያ 745ሺ እንዲሁም ለ266ሺ የዚምባቡዌ ገበሬዎች መድን ሽፋን የሚውል ነው ተብሏል፡፡

የቡድን 7 አባል አገራት እ.ኤ.አ እስከ 2025 ድረስ ተጋላጭ መድን ባሉት ድጋፍ ለአደጋ ተገላጭና ችግረኛ አፍሪካውያን ገበሬዎችን ለመደገፍ ድጋፍ 500 መሊዮን ዶላር መመደባቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም