በህንድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በገጠራማ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው ተባለ

72

ሰኔ 15/2012(ኢዜአ) የኮሮና ቫይረስ የህንድን ዋና ዋና ከተሞች በስፋት ካዳረሰ በኋላ 70 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ህዝብ ወደ ሚኖርበት የገጠሩ ክፍል እየተስፋፋ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በተለያዩ ከተሞች ስራ ላይ የነበሩ በሚሊዬን የሚቆጠሩ  ሰዎች መንግስት ከተሞች እንዲዘጉ በማድረጉ ሳቢያ ምክንያት ስራ አጥ በመሆናቸው ወደ አገሩቱ ገጠራማ አካባቢዎች መመለሳቸውን የብሉምበርግ ዘገባ ያመለክታል።

በመሆኑም የገጠራማ አካባቢዎች ለወረርሸኙ ስርጭት ተጋላጭነት መጨመሩ ነው በዘገባው የተጠቀሰው።

በአሁኑ ወቅት  ቫይረሱ 98 በመቶ የሚሆኑት የህንድ ገጠራማ አካባቢዎች መስፋፋቱ ተገልጿል።

በአካባቢዎቹም  የጤና መሰረተ ልማቶችና የኑሮ ሁኔታዎች ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆኑ ለወረርሽኑ መስፋፋትና የሟቾች ቁጥር ከመጨመሩ  አንጻር ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ህንድ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከአለም በአራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ቫይረሱ በአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች እየተስፋፋ መሆኑ  ስርጭቱን ሊያባብሰው እንደሚችል በዘገባው ተመልክቷል።