በመዲናዋ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3ሺህ 105 ደረሰ

211

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14/2012(ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓታት በአገር አቀፍ ደረጃ ከተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ 31 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የከተማው ጤና ቢሮ አስታውቋል።

በዚህም በከተማዋ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3ሺህ 105 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ከኮሮናቫይረስ ጋር በተገናኘ በሕክምና ማእከል ውስጥ የነበሩ የአንዲት ሴት ሕይወት ማለፉም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትናንትናው ዕለት 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮናቫይረስ ሕመም አገግመዋል።