ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከመከላከያ ሠራዊት ጄነራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ

271

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመከላከያ ሠራዊት ጄነራል መኮንኖች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመከላከያ ሠራዊት ጄነራል መኮንኖች ጋር  ያደረጉት ውይይት በአዲሱ የመከላከያ ግንባታ ስትራቴጂ ዝግጅት እና በተቋማዊ የግንባታ ሂደት ላይ ያተኮረ ነበር።

በዚህም ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።