በኢትዮጵያ ተጨማሪ 63 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 2 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

142

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14/2012(ኢዜአ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4457 የላቦራቶሪ ምርመራ 63 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 31 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 4 ሰዎች ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 3 ሰዎች ከኣማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል እና 1 ሰው ከሀረሪ ክልል መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው 42 ወንዶች እና 21 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ14 እስከ 76 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።

ከዚህ በተጨማሪ በለይቶ በህክምና ማዕክል ውስጥ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዜጎች ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል።

በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 91 ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ፣ 16 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 1213 አድርሶታል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 3243 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 32 በፀና የታመሙ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካሁን 216 ሺህ 328 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም