የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

89

አክሱም  ሰኔ 13/2012 (ኢዜአ) የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ከ700 በላይ ወገኖች 250 ኩንታል እህል ድጋፍ አደረጉ።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ገብረመድህን መዝገበ እንደገለጹት ድጋፉ  የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ  ከወርሀዊ ደሞዛቸው በመቀነስ ባዋጡት ገንዘብ የተገዛ ነው ።

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በ375 ሺህ ብር የገዛው 250 ኩንታል በዓድዋ፣አክሱም ሸራሮ ከተሞች ለሚገኙ የተቸገሩ ወገኖች እንዲደርስ አድርገዋል ።

 ባለፈው ወርም 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው እህል በትግራይ ማዕከላዊ፣ሰሜናዊ ምዕራብ እና ምዕራብ ዞኖች ለሚገኙ ለተቸገሩ ወገኖች ማከፋፈሉን ይታወቃል።

የዓድዋ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ ተክላይ ፍስሃ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ያደረገው ድጋፍ ማህበራዊና ሰብአዊ ሃላፊነቱን ስለሚሰማው ለተቸገሩ ወገኖቹ  ደራሽ ሆኗል ።

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል የዓድዋ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ዘቢባ ሃሰን በሰጡት አስተያየት በበሽታው ምክንያት ተንቀሳቅሶ መስራት ያልቻለ ብዙ ማህበረሰብ  ቤት ውስጥ መቀመጡን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው  ለሶስት ልጆቸው ጭምር አንድ ኩንታል እህል እንደሰጣቸው ጠቅሰው ምስጋናቸውን የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም