በደቡብ አፍሪካ 2 ሚሊዮን ሌትር ነዳጅ መሰረቁ ተሰማ

79

ሰኔ 11/2012(ኢዜአ) በደቡብ አፍሪካ በነዳጅ ማሰተላለፊያ ቱቦዎች ላይ በተፈጸመ ዘረፋ 2 ሚሊዮን ነዳጅ መሰረቁ ተነግሯል፡፡

የደቡብ አፍሪካ የነዳጅ ዘይት ኢንዱስትሪ ማህበር በድኅረ ገጹ በኩል እንዳስታወቀው በደቡብ አፍሪካ ካለፉት  ወራት ወዲህ በተደራጀ ሁኔታ የነዳጅ ስርቆት ተበራክቷል፡፡

ከሚያዚያ ወር ጀምሮ በተፈጸሙ 26 ዘረፋዎችም 2 ሚሊዮን ሌትር ገደማ የነዳጅ ዘይት መሰረቁን ነው ይፋ ያደረገው፡፡

በደበቡብ አፍሪካ በሚገኙ አንዳንድ ግዛቶች የተከሰተው የነዳጅ  እጥረት ለስርቆቱ  መነሻ ሳይሆን አይረቀርም ተብሏል፡፡

የአገሪቱ ፖሊስ በበኩሉ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ተጠርጣሪዎቹን ማሰሩን ገልጾ የተፈጠረውን የነዳጅ እጠረት የሚቀርፉ ማጓጓዣዎች መዘጋጀታቸውን አስታውቋል፡፡

በግንቦት ወር ብቻ ኮሮና ባስከተለው የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት 30 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ነዳጅ የማጣራት አቅም መስተጓጎሉ ተዘግቧል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም