የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ ነገ ይጀመራል

60

ሐዋሳ፣ ሰኔ 10/2012 ( ኢዜአ) የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባዔ ነገ በሀዋሳ ከተማ እንደሚጀመር ተገለጸ።

የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወይዘሮ ዓለሚቱ አበበ ለኢዜአ እንደተናገሩት የምክር ቤቱ ጉባዔ ከሰኔ 11/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

የጉባዔው አጀንዳ ነገ የምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት ይፋ እንደሚደረግ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም