በአርባ ምንጭ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተጀመረ

83

አርባ ምንጭ፣ ሰኔ 06//2012 (ኢዜአ) በአርባ ምንጭ ከተማ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የምርመራ  ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀመረ።

የምርመራው ሥራ የተጀመረው በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል  በተዘጋጀ ማዕከል ውስጥ ነው።

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ በዚህ ወቅት እንዳስታወቁት ማዕከሉ በቀን እስከ 400 ሰዎችን ለመመርመር የሚያስችል ነው።

ማዕከሉ ለጋሞ፣ ጎፋ፣ ኮንሶና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እንዲሁም ለባስከቶ፣ ደራሼና አሌ ልዩ ወረዳዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

በአርባ ምንጭ ሆስፒታል ማዕከል የምርመራው ሥራ መጀመሩ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

የምርመራ ማዕከሉ ከሐዋሳና ወላይታ ሶዶ ቀጥሎ በደቡብ ክልል ሦስተኛው እንደሆነም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም