በመዲናዋ 2 ዘመናዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ ነው

75

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/2012(ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ሁለት ዘመናዊ ሆስፒታሎች ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በሆስፒታሎቹ የዲዛይን እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ሆስፒታሎቹን በንፍስ ስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ግንባታቸውን ለማካሄድ የዲዛይን እና የመሬት ዝግጅት የማድረግ ሥራ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ በውይይቱ ተገልጿል፡፡

በከተማዋ የታካሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የሆስፒታሎችን ቁጥር መጨመር አስፈላጊ መሆኑን ኢንጂኒየር ታከለ ዑማ ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ ስድስት የመንግሥት ሆስፒታሎች የሚገኙ ሲሆን 1557 አልጋዎች ብቻ ይዘዋል፡፡

የሁለቱ ሆስፒታሎች ግንባታ ሲጠናቀቅም ተጨማሪ 940 አልጋዎች ይኖራቸዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም