በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣው መግለጫ በመጣራት ላይ ነው... ጠቅላይ አቃቤ ሕግ

48

ግንቦት 25/2012(ኢዜአ) በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የወጣው መግለጫ እንደተመለከቱት እና በመጣራት ላይ እንደሚገኝም ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አበቤ አስታወቁ።

የማጣራት ስራ ተጠናቆ ምላሽ ለመስጠት በሂደት እያለ መግለጫው በተለያዩ ሚዲያ መሰራጨቱን ገልፀዋል፡:

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች በማህበራዊ ገፃቸው እንደገለፁት "ሰብዓዊ መብት የምናከብረው እና የምናስከብረው ለማንም ብለን ሳይሆን ለህዝባችን እና ለፍትህ ስንል ነው" ብለዋል።

"አሁንም ቢሆን ዘገባዉን ከይዘቱ፣ ከአካሄዱ፣ እንዲሁም የጉዳዩን እውነተኛነት እና ገለልተኛነት የማጣራት ስራችንን በቶሎ ለማጠናቀቅ እየሰራን ነው" ነው ያሉት።

"በማጣራት ስራችን በሚገኘውም ውጤት፣ሪፖርቱ እውነት በሆነበት ልክ፣ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች እንወስዳለን" ብለዋል።

ሀሰት በሆነበት ወይም በተጋነነበት አኳያ ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋራ በመወያየት ሪፖርቱ እንዲስተካከል ጥረት እንደሚደረግም ከጠቅላይ አቃቤ ሕጓ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ይህ ባይቻል እንኳን ህዝባችንና አለም እውነቱን እንዲያውቀዉ በመረጃ አስደግፈን እናሳያለን በማለት ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም