109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

60

አዲስ አበባ  ግንቦት 23/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ  2836 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው  የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህም  በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 1172 አድርሶታል።

 የጤና ሚኒስትሯ  ዶክተር ሊያ ታደስ  እንደገለፁት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠው እድሜያቸው ከ5 እስከ 70 ዓመት ነው፡፡

በምርመራ ከተረጋገጠው 61 ወንድና 48 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸውም  99 ኙ ከአዲስ አበባ፣2ቱ ከትግራይ ክልል፤5 ኦሮሚያ ክልል እና 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 2 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው 13 እንዲሁም 94 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው እለት የሶስት ኢትዮጵያውያን ሕይወት ማለፉም ታውቋል፡፡

በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 11 ደርሷል፡፡

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 950 ናቸው።

ተጨማሪ 1 ሰው ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 209 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አራት ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል።

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 109 ሺህ 451 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

የጤና ሚኒስቴር  ህይወታቸው ባለፉት ሰዎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም