የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አባላት ደም ለገሱ

62

አዲስ  አበባ  ግንቦት 21/2012 (ኢዜአ) ከአዲስ አበባ አስተዳደር አስር ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ 140 የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አባላት ደም ለገሱ።

በደም እጥረት  የሚደረሰውን ጉዳትና የሕይወት መጥፋት ለመቀነስ ደም መለገሳቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መላኬ አለማየሁ ገልጸዋል።

በኮሮና ቫይረስ  የደም እጥረት እንዳይከሰትና በተለይም ደግሞ ሴቶች እንዳይጎዱ የሊጉ አባላት  ለሁለተኛ ጊዜ ደም መለገሳቸውንም ተናግረዋል።

ከሊጉ አባላት ወይዘሮ ኢትዮጵያ ታመነ  ና ወይዘሮ ማርታ ጌታቸው ደም በመለገስ ሕይወት ማዳን በጎ ተግባር በመሆኑ ‘ደም እየሰጠን ነው’ ሲሉ ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ርቀታችንን ጠብቀን ደም ለመስጠት መጥተናልም ብለዋል።