በአዲስ አበባ ከተማ 552 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

61

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ 552 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የከተማው አስተዳደር ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

ቢሮው በፌስ ቡክ ባሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው በከተማዋ በቫይረሱ የተያያዙ ሰዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች  ይገኛሉ።

ነዋሪዎች የቫይረሱ  ሥርጭት  እየተስፋፋ በመሆኑ  ተገቢውን  ጥንቃቄ እንዲያደርጉም   ቢሮው አሳስቧል።

 በቫይረሱ የተያዙ  21 ሰዎች  አድራሻቸውም በመጣራት ላይ እንደሆነም ገልጿል።

በከተማዋ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች በክፍለ ከተማ ደረጃ ሲተነትን በአዲስ ከተማ 138፣ በልደታ 133፣ በቦሌ 62 ተገኝተዋል።

ጉለሌ 44፣ ኮልፌ ቀራኒዮ 47፣.ንፋስ ስልክ ላፍቶ  ደግሞ 29 ሰዎችን አስመዝግበዋል።

የካ 26፣ አራዳ 23፣ አቃቂ ቃሊቲ 21 እና ቂርቆስ 19 ሰዎች ቫይረሱ  እንደተገኘባቸው   ቢሮው አመልክቷል።

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 100 ሰዎች 94ቱ የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ  በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 831 የደረሰ ሲሆን፤ አዲስ አበባ ከፍተኛ ቁጥር መያዙን  የጤና ሚኒስቴር መረጃ  ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም