የፌዴራልና የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች በደብረ ማርቆስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው

137

ደብረ ማርቆስ ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና በኢፌዲሪ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር የተመራ የልዑካን ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን መጎብኘት ጀመሩ።

በርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህና በኮሚሽነር አበበ አበባየሁ ጥሩነህ የተመራው የልዑካን ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነባ ያለውን የዘይት ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

በከፍተኛ አመራሩ የተጎበኘው የዘይት ፋብሪካ አቶ ወርቁ አይተነው በተባሉ ባለሀብት በሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እየተገነባ ሲሆን ግንባታውም 95 በመቶ ተጠናቋል ተብሏል።

የዘይት ፋብሪካው በቅርቡ ወደ ማምረት ሲገባም በቀን 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ገበያ ያቀርባል ተብሏል።

የከፍተኛ አመራሩ ጉብኝትም በኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመገምገም ማስተካከያዎችን ለማድረግ ያለመ ነው።

በጉብኝቱም ከርዕሰ መስተዳደሩና ኮሚሽነሩ በተጨማሪ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።