በጋምቤላ 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ችግኝ ለተከላ ተዘጋጅቷል

539

ጋምቤላ ግንቦት 19 / 2012 ዓም  በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የክረምት ወራት የሚተከል 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ባለፈው ክረምት ከተተከሉት 3 ሚሊዮን ችግኞች መካከል ከ80 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መጽደቃቸውንም ቢሮው ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ለው ኡቡፕ የተዘጋጁ ችግኞችን ለክልሉ ከፍተኛ ኃላፊዎችን በአስጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት ለተካላ የተዘጋጁት ችግች የተለያዩ ኢኮኖሚዊ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬና የጥላ ዛፍ ችግኞች ናቸው።

በዘንድሮው ዓመት እንደ ሀገር በታለመው የአረንጓዴ ልማት አሻራ ክልሉ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ድርሻ የነበረው ቢሆንም እቅዱን ከእጥፍ በላይ ማሳደጉን ገልጸዋል።

በአምስት የልማት ፕሮጀክቶች ለተከላ የተዘጋጁት ችግኞች ካለፈው ዓመት በ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብልጫ እንዳለቻው ጠቁመው ችግኞችን የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ለመትከል ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ባለፈው ዓመት በአረንጓዴ አሻራና በሌሎች መረሃ ግብሮች ከተተኩለት ከ3 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ከ80 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መጽደቃቸውንም የቢሮው ኃላፊ ገልጸዋል።

በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት የዘላቂ መሬት አያያዝና አጠቀቀም ፕሮጀከት አስተባበሪ አቶ ሙላት ቢረጋ እንደሚሉት ደግሞ በዘንደሮው ዓመት እርሳቸው በሚመሩት ፕሮጀክት ብቻ በ16 የችግኝ ማፍያ ጣቢያዎች 3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ችግኞች ለተከላ ተዘጋጀተዋል ።

በፕሮጀክቱ ከተፈሉት ችግኞች መካከል ቡና፣ አቡካዶ፣ ማንጎና ሌሎች የፍራፈሬና የጥላ ዛፍ ችግኞች እንደሚገኙበት ገልዋል።

ፕሮጀክቱ በዘንደሮው ዓመት ከአቅድ በላይ ችግኞችን ማፍላቱን ጠቁመው ይህም ሊሆን የቻለው በበጋው ወራት በ3 ሺህ 800 የተራቆተ ሄክታር መሬት ላይ በተሰራው የተፋሰስ ልማት ለመትከል አመቺ ሁኔታ በመፈጠሩ ነው ብለዋል ።