በአማራ ክልል የተቋማት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል

150

ባህርዳር (ኢዜአ) የአማራ ክልል የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች እቅድ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ   ተጀመረ።

የክልሉ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ በድሉ ድንገቱ እንደገለጹት የክልሉ ተቋማት አመራሮች የሚሳተፉበት ይህ መድረክ በኢኮኖሚ በልማትና በማህበራዊ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ይገመገሙበታል።

እንዲሁም በመልካም አስተዳደርና ፍትህ ስራዎች ዙሪያ ያሉ ጥንካሬና ድክመቶችን ተለይተው በሚቀርቡ የመፍትሔ ሃሳቦች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በተቋማቱ አሰራሮች ላይ ያጋጠሙ ክፍተቶች ላይም በክልሉ ርዕሰ-መስትዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። 

ለአንድ ቀን በሚካሔደው በዚህ መድረክ ላይ ርዕሰ-መስተዳደሩን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ ተቋማት ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።